እየተካሄደ ያለው የ20/80 እና የ40/60 አማራጭ የማህበር መኖሪያ ቤት ምዝገባ ተራዘመ

324

ሚያዚያ 6 /2013 (ኢዜአ) እየተካሄደ ያለው የ20/80 እና የ40/60 አማራጭ የማህበር የመኖሪያ ቤት ምዝገባ ለተጨማሪ 10 ቀናት መራዘሙን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው እንዳስታወቀው፤ ምዝገባው እንዲራዘም የተደረገው ከህብረተሰቡ በቀረበ ጥያቄ መሰረት ነው።

በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና በ40/60 አማራጮች ከተመዘገቡት ቤት ፈላጊዎች ውስጥ አቅምና ፍላጎት ያላቸው በጋራ ሕንፃ መኖሪያ ቤት በህብረት ሥራ ማህበር ተደራጅተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ አዲስ አሰራር ተዘርግቷል።

በመንግስት ተዘጋጅቶ በሚቀርብ መሬት የቁጠባ ሂሳባቸውን ያልዘጉ ተመዝጋቢዎች 70 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ በመፈጸም በማህበር ተደራጅተው የመኖሪያ ህንጻዎችን መገንባት እንደሚችሉም አሰራር መዘርጋቱ ይታወሳል። 

ምዝገባውም ከመጋቢት 21 እስከ ሚያዚያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ለተከታታይ 15 ቀናት ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።

በምዝገባውም እስካሁን ከ8 ሺህ 500 በላይ የማህበር ቤት ፈላጊዎች መመዝገባቸውን አስታውቋል።

በተለየ ምክንያት ምዝገባውን ያልሰሙ የአማራጭ ቤት ልማት ፕሮግራሙ ፈላጊዎች በመኖራቸው ተጨማሪ እድል ለመስጠት ሲባል የምዝገባ ጊዜውን ማራዘም አስፈላጊ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።

በመሆኑም ተመዝጋቢዎች ከሚያዚያ 6 እስከ 15 ቀን 2013 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን አውቀው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ እንዲመዘገቡ ጠይቀዋል።

ለመመዝገብ እየፈለጉ በሲስተም መጨናነቅ ምክንያት ላልተመዘገቡና ከመረጃው ማዳረስ አንጻር ተጠቃሚው በቂ ግንዛቤ ባለመያዙ ቀኑ ተራዝሟል።

ተመዝጋቢዎች በማህበራዊ ትስስር ገጽ በቢሮው አድራሻ WWW.aahdab.gov.et ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም