ለምስራቅ አፍሪካ አባል ሃገራት ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች በሰላም ማስከበር ዙሪያ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

67

ሚያዚያ 4/2013 ( ኢዜአለምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል አባል ሃገራት ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች በሰላም ማስከበር ቅድመ ስምሪት ዙሪያ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።

የከፍተኛ መኮንኖቹ ስልጠና መሰጠት የጀመረው ሰንዳፋ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ነው።

በስልጠናው ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ7 ሀገራት የተውጣጡ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች የተገኙ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

በስልጠናው ከኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳ ፣ ኮሞሮስ ፣ ጅቡቲ ፣ ሶማሊያ ፣ ኬኒያ እና ብሩንዲ የተውጣጡ የፖሊስ መኮንኖች እየተሣተፉ ነው፡፡

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል ዳይሬክተር ብርጋዴል ጀነራል ጌታቸው ሽፈራው እንዳሉት ስልጠናው ለቀጣናው የጋራ ሰላም፣ ዕድገትና የጋራ ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

በመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል።

የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል 10 አባል ሃገራትን በውስጡ የያዘ መሆኑም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም