ፖፕ ፍራንሲስ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለድሆች ጭምር ተደራሽ እንዲሆን ጥሪ አቀረቡ

91

መጋቢት 27 ቀን 2013 (ኢዜአ) የሮማው ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለድሃ አገራት ጭምር ተደራሽ እንዲሆን ለአለም ማኅበረሰብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፖፕ ፍራንሲስ ይህን ያሉት በቅርቡ የሚከበረውን የትንሳዔ በዓል አስመልክቶ ለህዝበ ክርስቲያኑ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ነው፡፡

ፖፕ ፍራንሲስ ክትባቱን የመግዛት አቅም ለሌላቸው አካላት ምንም አይነት ልዩነት ሳይደረግ ተደራሽ እንዲሆንላቸው ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡

በተለይ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ልዩ ትኩረት ያስፈልጋቸዋል ማለታቸውን ዘ ታይምስ መጽሄት አስነብቧል፡፡

84 አመት የሞላቸው ፖፕ ፍራንሲስ ክትባቱን የወሰዱ ሲሆን ቫቲካን ለድሃ የህብረተሰብ ክፍሎችና ጎዳና ተዳዳሪዎች መከተብ መጀመሯን ተናግረዋል፡፡

ለተጋላጭ የህብረተብ ክፍሎች እና አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢው ትኩረት ካልተሰጠ የሚያስከትለው ተጽዕኖ ቀላል እንደማይሆን ጠቁመው፤ ለክትባቱ ተደራሽነት ሃብታም ሃገራት ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

"በመጨረሻም በተከሰተው ወረርሽኝ ሳቢያ ለሚሰቃዩት ሁሉ ክርስቶስ ተስፋ እና መጽናናትን ይስጥ" ብለዋል፡፡


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም