በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ

92

መጋቢት22/2013 ነቀምቴ / ኢዜአ/ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የመረጃ ክፍል ባለሙያ ሳጂን ኦላና ተክሉ ለኢዜአ እንደገለጹት የጦር መሳሪያው የተያዘው በዞኑ በአሙሩ ወረዳ በአገምሣ ፍተሻ ኬላ ላይ ነው።

በወረዳውና በክልሉ ልዩ ሀይል ፖሊሶች በተደረገ ፍተሻ የጦር መሳሪያው መያዙን ተናግረዋል ።

በፍተሻው ከተያዙት የጦር መሳሪያዎች ሶስት ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፣ 16 ቱርከ ሰራሽ ሽጉጦችና 5ሺህ 855 የክላሽ፣ የብሬልና የሽጉጥ ተተኳሽ ጥይቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በጦር መሳሪያዎቹ ዝውውር የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን አስታውቀዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም