የኢንጂነር ስመኘው በቀለ የቀብር ሥነ-ስርዓት ተፈጸመ

73
አዲስ አበባ ሀምሌ22/2010 የኢንጂነር ስመኘው በቀለ የቀብር ሥነ-ስርዓት ተፈጸመ። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ የነበሩት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ስርዓተ-ቀብር ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ተፈጽሟል። በስነ-ስርዓቱ ላይ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ሙፈሪያት ካሚል፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ተገኝተዋል። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓም ነው በጥይት ተመትተው በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ሞተው የተገኙ ሲሆን ፖሊስ የአሟሟታቸውን መንስኤ በመመርመር ላይ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም