የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና ግብጽ የሶስትዮሽ ውይይት በአዲስ አበባ ተጀምሯል

72
አዲስ አበባ ግንቦት 7/2010 የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብጽ  የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሮች እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ውይይት በአዲስ አበባ ተጀምሯል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ኢትዮጵያ ውይይቱን በሙሉ ልቧ እንደምታካሄድ በዚሁ ጊዜ ጠቅሰው፤ በውይይቱ በብዙ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት እንደሚደረስም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። አጠቃላይ የውሃ አጠቃቀም አስመልክቶ  በአዲስ አበባ በተካሄደው 18ኛው የሶስትዮሽ ውይይት ላይ  ከስምምነት ያልተደረሱባቸውና አሁን መግባባት ሊደረስባቸው ይችላል ተብለው የሚጠበቁ ነጥቦች ላይ ውይይት እየተደረገ እንደሆነም ዶክተር ወርቅነህ ገልጸዋል። ከወር በፊት በሱዳን በተካሄደው የሶስትዮሽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውይይት ላይ አገራቱ በጋራ የመሰረተ ልማት ግንባታና በሌሎች ጉዳዮችም ላይ ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም