የካቢኔ ስብሰባ ወደ ቅዳሜ ተዛወረ

74
አዲስ አበባ ግንቦት 7/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አርብ ይካሄድ የነበረው የካቢኔ ስብሰባ ወደ ቅዳሜ እንዲዛወር አደረጉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጉዳይ ላይ ዛሬ ለመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ገለጻ አድርገዋል። ከዚህ በፊት የስብሰባዎች መብዛትና መንዛዛት የመንግስት የስራ ጊዜ ላይ ተጽዕኖ እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል። በመሆኑም የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ስብሰባ ከስራ ሰዓት ውጪ መሆን እንደሚገባው ተናግረው ነበር። በዚሁ መሰረት ዛሬ ባደረጉት ገለጻ ከዚህ በፊት በየሳምንቱ አርብ ጠዋት በስራ ሰዓት ሲካሄድ የነበረው የካቢኔ ስብሰባ ወደ ቅዳሜ ጠዋት እንደሚዛወር አስታውቀዋል። በስብሰባ ላይ በማይገባ ክርክርና ጭቅጭቅ የሚባክኑ ሰዓቶችን ለመቀነስ ጥረት እንደሚደረግም አክለዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም