ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከጂቡቲ ወደ አገራቸው ተመለሱ

71
አዲስ አበባ ሃምሌ 20/2010 185 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከጂቡቲ ወደ አገራቸው ተመለሱ። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በደላሎች አማካኝነት በሕገ-ወጥ መንገድ ወደተለያዩ የአረብ አገራት ለመሄድ የጂቡቲን ድንበር አቋርጠው የገቡ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ስደተኞቹ በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የጋራ ጥረት ትናንት ወደ አገራቸው መግባታቸው ተገልጿል። በሰኔ 2010 ዓ.ም ከ360 በላይ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከጂቡቲ ወደ አገራቸው መመለሳቸው የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ መንግስትና ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በጋራ በተለያዩ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እያደረጉ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም