በአማራ ክልል ከ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተያዘላቸው ሁለት መንገዶች ግንባታ ዛሬ ይጀመራል

71

የካቲት 22/2013(ኢዜአ) በአማራ ክልል ከ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተያዘላቸው ሁለት መንገዶች ዛሬ ግንባታቸው ይጀመራል።

ፕሮጀክቶቹ የደንበጫ-ሰቀላ ሎት አንድ እንዲሁም የዓርብ ገበያ-ሰከላ-ቲሊሊ ምዕራፍ ሁለት የአስፋልት ኮንክሪት መንገዶች ናቸው።

ሁለቱ የመንገድ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ 132 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው ሲሆኑ የግንባታቸው ወጪ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው።

የደንበጫ-ሰቀላ ሎት አንድ እና የዓርብ ገበያ-ሰከላ-ቲሊሊ ምዕራፍ ሁለት የአስፋልት ኮንክሪት ፕሮጀክቶች የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ገልጿል።

በግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኝሁ ተሻገር እና የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ እንደሚገኙ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም