የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክትና ማኑፌስቶውን በአርባ ምንጭ እያስተዋወቀ ነው

60

አርባምንጭ የካቲት 17 2013 (ኢዜአ) የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክትና ማኑፌስቶውን የማስተዋወቂያ ስነ ስርአት በአርባምንጭ ከተማ እያካሄደ ነው።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎና ሌሎች በፌዴራልና በክልል ደረጃ የሚገኙ የደቡብ ክልል ክፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ፓርቲው በዛሬው ስነ-ስርዓት ከምርጫ ምልክትና ማኑፌስቶውን ከማስተዋወቅ ጎን ለጎን የምረጡኝ ቅስቀሳውን በይፋ ይጀመራል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም