ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ከኔዘርላንድስ አቻቸው ጋር ተወያዩ

የካቲት 10 /2013 (ኢዜአ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።

መሪዎቹ ከአገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት በተጨማሪ በቀጠናዊ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ኢትዮጵያ ከኔዘርላንድስ ጋር ለረጅም ጊዜ የቆየ ጠንካራ የንግድ፣ የዲፕሎማሲና የኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አስታውቀዋል።


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም