የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በአድዋ በዓል ላይ ለመታደም ጋምቤላ ከተማ ገቡ

97

ጋምቤላ፣ የካቲት 09 /2013 (ኢዜአ) በጋምቤላ ክልል ደረጃ ነገ በሚከበረው የአድዋ 125ኛ ክብር በዓል ላይ ለመታደም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክትር ሂሩት ካሳው ዛሬ ጋምቤላ ከተማ ገቡ።

ሚኒስትሯ ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደረሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዶክተር ሂሩት ማምሻቸውን ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆኑን በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችና በከተማዋ ለአደዋ ፓርክነት የተመረጠውን ቦታ እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።

ነገ ደግሞ 'አድዋ የህብረ-ብሔራዊ አንድነት አርማ' በሚል መሪ ሀሳብ በክልል ደረጃ በሚከበረው በዓል ላይ እንደሚታደሙ የኢዜአ ሪፖርተር ከጋምቤላ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም