በቱርክ አንካራ አዲሱ ኤምባሲ ተመረቀ

769

የካቲት 8 / 2013 (ኢዜአ) የኢፌዲሪ ኤምባሲ በቱርክ አንካራ ከፍተኛ የመንግሰት ባለሥልጣናት በተገኙበት ዛሬ አዲስ ህንጻ አስመረቋል፡፡

በምርቃት ሰነ ሥርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የቱርኩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቩልት ካቩሶግሉ ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅት የቱርኩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቩልት ካቩሶግሉ እንዳሉት ቱርክ የአፍሪካ አገራትን በመደገፍ ከአገራቱ ጋር በኢኮኖሚ፣ በሰላምና ደህንነት ያላትን ግንኙነት ታጠናክራለች።

በዛሬው እለት የተመረቀው አዲሱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ህንጻም የአገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አመልክተዋል።

ኢትዮጵያና ቱርክ 125 ዓመታት የዘለቀ ጠንካራ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።