ግብረ ሰናይ ድርጅቱ በትግራይ ድጋፍ ለሚሹ ወገኞች ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ዓልሚ ምግብ አበረከተ

70

መቀሌ፣ የካቲት 8/2013 ( ኢዜአ)  ሰማሪታንስ ፐርስ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በትግራይ ክልል ሠብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ዓልሚ ምግብ አደረሰ፡፡

ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤቱ ከሚገኝበት ኖርዝ ካሮላይና ግዛት ቡን ከተማ በራሱ የዕቃ ጫኝ አውሮፕላን የላከው የምግብ ቁሳቁስ ዛሬ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ ደርሶ ተራግፏል፡፡ 

ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ከዋና መስሪያ ቤቱ ኖርዝ ካሮላይና የላከው አልሚ ምግብ 310 ኩንታል መሆኑ ታውቋል፡፡

አልሚ ምግቡ በትግራይ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው ሕጻናት፣ ለነፍሰ ጡር እና ለሚያጠቡ እናቶች የሚውል ነው፡፡

ድጋፉን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ገብረሕይወትና የካቢኔ አባላት ተረክበዋል።

ሰማሪታንስ ፐርስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ በበጎ አድራጎት ምዝገባ ቁጥር 4046 ተመዝግቦ የበጎ አድራጎት ስራውን በመከወን ላይ እንደሚገኝ ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም