ጅማ ዩኒቨርስቲ 4ሺህ 311 ተማሪዎችን ነገ ያስመርቃል

183

የካቲት 05/2013 (ኢዜአ) ጅማ ዩኒቨርስቲ በሁለተኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 4ሺህ 311 ተማሪዎችን ነገ እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡

የዩኒቨርስቲው ሪጅስትራር ጽህፈት ቤት ሲኒየር ዳይሬክተር አቶ ብሩክ ወልደ ሚካኤል ለኢዜአ እንዳሉት ነገ ከሚመረቁት ተማሪዎች መካከል 3ሺህ 950 በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ከእነዚህም  ውስጥ 1ሺህ 530 ሴቶች ናቸው።

በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ 45 ሴቶች የሚገኙበት 354  ተማሪዎች ይመረቃሉ ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ  ገለጻ ሶሰት ተማሪዎች በሶስተኛ ዲግሪ እና አራት  ተማሪዎች ደግሞ የ "ሰብ ስፔሻሊቲ" ተመራቂ ይሆናሉ።

በምርቃት ሂደቱ ኮሮናን ለመከላከል የሚያግዙ ግብአቶች መዘጋጀታቸውን የተናገሩት ደግሞ  የዩኒቨርስቲው  የውጭ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን  ሲኒየር ዳይሬክተር ዶክተር ወንድሙ ለገሰ ናቸው።

ከተሸላሚ ተማሪ  ወላጆች በስተቀር ሌሎች ቤተሰቦች በሌላ አዳራሽ ሥነ-ሥርዓቱን   በቀጥታ ሥርጭት ይከታተላሉ ብለዋል፡፡

ጅማ ዩኒቨርስቲ ባለፈው  ጥቅምት ወር  1ሺህ 409  ተማሪዎችን ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም