የዩኤንዲፒ አፍሪካ ቀጠናዊ ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ መቀሌ ገብተዋል

47

መቀሌ፣ የካቲት 3 ቀን 2013 (ኢዜአ) የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) የአፍሪካ ቀጠናዊ ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ መቀሌ ገብተዋል።

ዳይሬክተሯ መቀሌ የገቡት በትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በመንግስት እየተካሄደ ያለውን የመልሶ ግንባታ ለመደገፍ የሚያስችል ጉብኝት ለማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።

በመቀሌ በሚኖራቸው የአንድ ቀን ቆይታ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዩኤንዲፒ ለትግራይ ክልል ሶስት ተሽከርካሪዎችና ሌሎች የቢሮ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም