የአለም ጤና ድርጅት ለአዋቂዎች የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ

1160

የካቲት 3/2013 (ኢዜአ) ኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለአዋቂዎች ጥቅም ላይ ለማዋል ማሰቡን የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

ይህ የተነገረው በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በተካሄደው በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ በተደረገው የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ስብሰባ ላይ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት በሁሉም ዕድሜ ውስጥ ባሉ አዋቂዎች ላይ የኦክስፎርድ-አስትራዛኔካ ክትባት መጠቀሙን በቅርቡ ይደግፋል መባሉን ዘ ቴሌግራፍ ጋዜጣ አስነብቧል።

በደሃ ሀገሮች ውስጥ ክትባቶችን ለማቅረብ ያለመ የአለም የጤና ድርጅት ኮቫክስ ፕሮግራም ክትባቱን ለመጠቀም ምክረ ሀሳቦች ቀርበዋል ።

የዓለም የጤና ድርጅትም እንግሊዝ እንዳደረገችው ለሁለተኛ ጊዜ ክትባቱን እስከ 12 ሳምንታት ድረስ የማዘግየት ስትራቴጂን ይደግፋል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል፡፡