ተመድ ለኢትዮጵያ ልማት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል–የአፍሪካ ቀጠና የተመድ ልማት ፕሮግራም ኃላፊ

1368

የካቲት 2/2013 (ኢዜአ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ለኢትዮጵያ ልማት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአፍሪካ ቀጠና የተመድ ልማት ፕሮግራም ኃላፊ  አሁና ኢዝያኮንዋ ገለፁ ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአፍሪካ ቀጠና የተመድ ልማት ፕሮግራም ኃላፊ  አሁና ኢዝያኮንዋ ትላንት ማነጋገራቸው ለገልፇል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለዋና ዳይሬክተሯ በኢትዮጵያና በተመድ ልማት ፕሮግራም ትብብር፣በትግራይ ያለውን የሰብአዊ ዕርዳታና በቀጣይ የሚካሄደው 6ኛ ምርጫ ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል ፡፡

የአፍሪካ ቀጠና የተመድ ልማት ፕሮግራም ኃላፊ  አሁና ኢዝያኮንዋ በውይይቱ ወቅት  እንደገለፁት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት  ለኢትዮጵያ ልማት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀትል መግለፃቸውን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ቃልአቀባይ ፅህፈት ቤት ገልፇል፡፡

የተመድ ልማት ፕሮግራም ሀገሪቱ የራዕይ 2030 ግብ ለማሳካት እያደረገች ላለው ድጋፍ አድናቆት እንዳለቸው ተናግረው ፤የሀገር በቀል የልማት ዕቅድ እና የኮቪድ በሽታ ዘላቂ ልማት ትግበራ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ዙሪያ ለዳይሬክተርዋ አብራርተዋል፡፡

አቶ ደመቀ የህግ የማስከበር ዘመቻ የተጠናቀቀ በመሆኑ መንግሰት ሰብአዊ ዕርዳታ ለማዳረስ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተቋቋመው 92 የዕርዳታ ማሰራጫ ማዕከላት በኩል ለድጋፍ ፈላጊዎቹ ዕርዳታ ለማድረስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን በመግለጽ ፤መንግስት ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት ከሌሎች ዕርደታ ሰጭ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 እንደዚሁም የጥፋት ቡድኑ ያወደማቸውን መሠረተ ልማቶ መልሶ ለመገንባት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በቀጣይ የሚካሄደውን 6ኛ አገራዊ ምርጫ በተደረገላቸው ገለጻ አስመልክተው የተመድ ልማት ፕሮግራም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድን አቅም ግንባታ ድጋፍ በማድረግ አካታች ፣ ታማኝና ሰላማዊ ምርጫ እንዲደረግ ድርጅታቸው የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

ተመድ ለኢትዮጵያ ልማት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና በቀጣይ ከከፍተኛ መንግስት ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ በትግራይ ክልልም ጉብኝት ለማድረግ ዕቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡