የወላይታ ዞን ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያላቸውን ድጋፍ በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጹ ነው

1545

ሶዶ፣ የካቲት 1/2013 ( ኢዜአ) የወላይታ ዞን ነዋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው ።

በሶዶ ስታድየም እየተካሄደ ባለው ሰላማዊ ሰልፍ ከዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው።

ሰልፈኞቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የጁንታውን ቡድን ለማምከን የሰጡትን በሳል አመራር እናደንቃለን፣ አደናጋሪ አሉባልታዎችን በማክሸፍ ለለውጡ እንተጋለን፣ ታላቁ የለውጥ ጉዟችን በዶክተር አብይ አህመድ መሪነት ተጠናክሮ ይቀጥላል የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ድጋፋቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።