የወላይትኛ ሙዚቃ ዘፋኙ ኮይሻ ሴታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

132
አዲስ አበባ ግንቦት 6/2010 ቀዳሚው የወላይትኛ ዘፋኙ ኮይሻ ሴታ ከዚሕ ዓለም በሞት ተለየ። እንደዛሬው የወላይትኛ ዘፋኞች ከመብዛታቸው በፊት ካሴት ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳተመው ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ ነበር። በ1984 ዓ.ም በኢትዮ ሙዚቃ ቤት አማካይነት ለሕዝብ ያደረሰው የሙዚቃ ካሴት የወላይታን ሕዝብ ሙዚቃና ባሕል ያስተዋወቀ ነበር። ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ በባህል ሙዚቃው ዘርፍ ድንቅ አበርክቶት ነበረው። ኮይሻ ሴታ አዲስ የሙዚቃ ካሴት ስራውን ለአድማጮች ለማድረስ እየሞከረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። የኮይሻ ሴታ አስከሬን ቀብሩ ወደ ሚፈጸምበት ደቡብ ክልል፤ ወላይታ ሶዶ በጓደኞቹና በሙያ አጋሮቹ ድጋፍ እንዲሸኝ ተደርጓል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም