የህዳሴ ግድብ ዋንጫ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነበረውን ቆይታ አጠናቆ የሽኝት መርሐ ግብር እየተከናወነ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የህዳሴ ግድብ ዋንጫ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነበረውን ቆይታ አጠናቆ የሽኝት መርሐ ግብር እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 27 /2013 (ኢዜአ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ለተረኛው ክልል ለማስረከብ የሽኝት መርሐ ግብር እየተከናወነ ነው።
በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ እና የፌዴራልና የአስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ዋንጫው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በነበረው የ14 ወራት ቆይታ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተዘዋውሮ ህብረተሰቡን በስፋት ያሳተፈ የገቢ ማሰባሰቢያ መከናወኑ ይታወቃል።