ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ በዲቦራ ፋዉንዴሽን ማእከል የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቤት ግንባታ አስጀመሩ

102

አዲስ አበባ፤ ጥር 25/2013 (ኢዜአ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ በዲቦራ ፋዉንዴሽን ማእከል የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቤት ግንባታ አስጀመሩ።

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በትኩረት ሊሰራበት ካስቀመጣቸዉ አቅጣጫዎች አንዱ የአዕምሮ ጤና እንክብካቤ እና ደህንነት ነዉ፡፡

በመሆኑም በዲቦራ ፋዉንዴሽን ማእከል የአዕምሮ እድገት ዉስንነት ላለባቸዉ ህጻናት እና ወጣቶች አገልግሎት የሚዉል ትምህርት ቤት ለመገንባት ዛሬ የመሰረት ድንጋይ እና ግንባታ የማስጀመር ስነስርአት አካሂዷል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በዲቦራ ፋዉንዴሽን ለሚገነባዉ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቤት ፕሮጀክት 19 ሚሊዮን ብር የመደበ ሲሆን የፕሮጀክቱ የገንዘብ ምንጭ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለትምህርት ቤቶች ግንባታ ከሰጡት የመደመር መጽሀፍ ሽያጭ ነዉ፡፡

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው የመሰረተ ድንጋይ ካስቀመጡና የግንባታ ማስጀመር ስነስርዓት ካካሄዱ በኋላ በማእከሉ ችግኝ መትከላቸውን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም