ሀገር አቀፍ የስራ ዕድል ፈጠራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው

117

አርባምንጭ ጥር 24/2013 (ኢዜአ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለፋት ስድስት ወራት የስራ ዕድል ፈጠራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው የግምገማ መድረክ የፌደራል፣ የአስሩም ክልሎችና  ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የዘርፉ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው  ምክክር እንደሚካሄድባቸው ይጠበቃል።

በመድረኩ የክልሎች የኢተርፕራይዝና የስራ ዕድል ቢሮዎች ፣ የፌዴራል የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እንዲሁም የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ አመራሮችና የመገናኛ ብዙሃን ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም