በዛሬው 10ኛው ሳምንት ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ አዳማ ከተማ ሀዋሳን 3ለ 1 አሸነፈ

1518

ጅማ፣ ጥር 23 ፣2013 (ኢዜአ) በዛሬው አስረኛው ሳምንት በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርምየር ሊግ ጨዋታ አዳማ ከተማ ሀዋሳን 3ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

ለአዳማ ከተማ ሶስቱንም ጎሎች ያስቆጠረው አብዲሳ ጀማል ነው።

አብዲሳ ጀማል በ24ኛው፣ በ63ኛውና በ74ኝው ደቂቃ ጎሎቹን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል።

ብሩክ በየነ በ55ኛው ደቂቃ ብቸኛዋን ግብ ለሀዋሳ አስቆጥሯል።

አሁን ላይ ጅማ አባጅፋር ከወላይታ ዲቻ እየተጫወቱ ነዉ።

ትናንት ሰበታ ከተማ ከሀዲያ ሆሳእና ባዶ ለ ባዶአቻ  ያለወጤት ተለያይተዋል።

የፕሪሚየር ሊጉ የ10ኛው  ሳምንት ጨዋታ መርሀግብር ዛሬ ይጠናቀቃል።