አገልግሎቱ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር የሞከሩ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳሰበ

60

ጥር 17/2013 ( ኢዜአ) ሃሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሲሞክሩ የነበሩ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል፡፡

አገልገሎት መሥሪያ ቤቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ፤ ከዚህ በኋላ የሀሰት መረጃዎችንና አሉባልታዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾች በማሰራጨት የሀገርን ብሄራዊ ጥቅምና ህልውና ለመጉዳት እንዲሁም የህዝብን ሰላምና ደህንነት ስጋት ላይ ለመጣል የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ማስረጃዎችን በማጠናቀር በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በሀገር ላይ የሚቃጡ የፀጥታና የደህንነት ስጋቶችን በማስቀረት ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ከማንኛውም ጊዜ በላይ ከሁሉም የጸጥታና የደህንነት ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ እንደሚገኝ መግለጫው አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም