ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የስራ ጊዜያቸውን ካጠናቀቁት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ጋር ተወያዩ

1803

ጥር 17/2013 ( ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የስራ ጊዜያቸውን ካጠናቀቁት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ ጋር ተወያዩ።

አቶ ደመቀ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ “አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ በቆይታቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦ ከልብ እያመሰገንኩ፤ በቀጣይ ስምሪታቸው መልካሙን እመኛለሁ” ብለዋል።

“የሁለቱን ሃገራት ታሪካዊ ግንኙነት እና ስትራቴጂያዊ ትብብር በማጠናከር ተልዕኳቸው ስኬታማ ነበር” ሲሉም ገልጸዋል።