የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የሠላምና የልማት የጋራ መድረክ ማካሄድ ጀመሩ

1448

ጥር 17 ቀን 2013 (ኢዜአ) የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የሠላምና ልማት የጋራ መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄዱ ነው።

በመድረኩ የሁለቱ ክልሎች የአምስት ዓመት የልማት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችም ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በውይይቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሎች የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል።

በውይይቱ ማጠቃለያም ክልሎቹ በቀጣይ ለሚያከናውኗቸው የሠላምና የልማት ስራዎች የመግባቢያ ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሏል።