ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ እያስመረቀ ነው

1501

ሀዋሳ፣  ጥር 15/2013(ኢዜአ) ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሠለጠናቸው ከአንድ ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ እያስመረቀ ነው። 

ዩኒቨርሲቲው የሚያስመርቃቸው ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ የሠለጠኑ ናቸው።

በቀድሞ  ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ   የመሰረት ድንጋይ ተጥሎ ግንባታው የተጀመረው የወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተጠናቀቁት  የመጀመሪያ ምዕራፍ  ህንጻዎች ከአራት ዓመት በፊት የተቀበላቸውን ተማሪዎች ነው ዛሬ እያስመረቀ ያለው።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ  የፌዴራልና የደቡብ ክልል  አመራሮች ተገኝተዋል።