በሠላም መልሶ ግንባታና በሕግ ማስከበር ላይ ያተኮረ አገር አቀፍ ውይይት እየተካሄደ ነው

1501

አዲስ አበባ፣ ጥር 15/2013 (ኢዜአ) በሠላም መልሶ ግንባታና በሕግ ማስከበር ላይ ያተኮረ አገር አቀፍ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በስትራቴጂክ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት በተዘጋጀው በዚህ ውይይት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች፣ ምሑራን፣ የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች፣ የፌዴራልና የክልል ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።

በመድረኩ ሶስት የመነሻ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚካሄድባቸው ተመልክቷል።

በውይይቱ የሚገኙ ምክረ ሀሳቦች ለመንግስት በግብዓትነት እንደሚውሉም ተጠቁሟል።

በድህረ ግጭት የሚታዩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ሠብዓዊ ጉዳዮችን ማረም የሚያስችል ጥናታዊ ጽሁፍ በመድረኩ እየቀረበ ነው።

ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ ሠላምና መረጋጋት ይበልጥ እንዲጎለብት የሚያግዙ የግንዛቤና የክህሎት ማጎልበቻ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ ይታወቃል።