ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን 7 ሺህ 293 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን 7 ሺህ 293 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

ጥር 15/2013(ኢዜአ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 7ሺህ 293 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።
ዩኒቨርሲቲው እያሰመረቃቸው ያሉ ተማሪዎች በመደበኛ ፣ ተከታታይና ክረምት መረሃ ግብሮች ያሰለጠናቸው ናቸው።
ተማሪዎቹ የሰለጠኑት በቅድመና ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ሲሆን ከመካከላቸው 2ሺህ 489 ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

በምረቃው ሥነ-ሥርዓት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች መገኘታቸውን ሪፖርተራችን ከጎንደር ዘግቧል።