የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸሙን እየገመገመ ነው

308

ጥር 13/2013 ( ኢዜአ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸሙን በአዳማ ከተማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ እየገመገመ ይገኛል።

በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የተመለከተ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

ባለፉት ስድስት ወራት የክልሉ ጸጥታ አካላት ህግ በማስከበር ረገድ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ጉልህ እንደነበርም በመድረኩ ተነስቷል።

ውይይቱም ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ይሆናል።