ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት ከ25 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ

58

አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2013 (ኢዜአ) ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት አመቱ ስድስት ወራት ከ25 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ አጋማሽ በሚመለከት ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኩባንያው በተጠቀሰው ጊዜ 25 ነጥብ 57 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቀዋል።

ገቢው የዕቅዱ የ95 በመቶ ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን ያብራሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ እቅዱ ሙሉ ለሙሉ ያልተሳካው በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረው ችግር ሳቢያ መሆኑን አብራርተዋል።

ይህም ሆኖ ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ12 ነጥብ 3 በመቶ እድገት ማሳየቱን አስታውቀዋል።

የደንበኞች የቴሌኮም አጠቃቀምን ለማሳደግና ተሞክሯቸውን የሚያሻሽሉባቸው የኔትወርክ ማስፋፊያና የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያ መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በመሆኑም የደንበኞች ፍላጎትንና ወቅታዊነትን የተላበሱ 21 አዳዲስና 18 ነባር የአገር ውስጥና የዓለም አቀፍ አገልግሎቶችን በማሻሻል ለደንበኞች ማድረሱን አብራርተዋል።

ገቢው በአገልግሎት አይነት ሲታይ 48 በመቶ የሚሆነው ከሞባይል ድምጽ የተገኘ ሲሆን፣ ኢንተርኔት 23 ነጥብ 3 በመቶ ድርሻ እንዳለው አንስተዋል።

የውጭ ምንዛሪ ግኝቱም 80 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን የጠቀሱት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ5 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ታይቶበታል ብለዋል።

ዕድገቱ የተመዘገበው አዳዲስ የገቢ ምንጮችን በመተግበርና የውጪ ምንዛሪ የሚያሳጡ የቴሌኮም ማጭበርበር ተግባራትን በመከላከል እንደሆነም አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ የሞባይልና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር እድገት እያሳየ መሆኑን ጠቅሰው ከሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች መካከል 64 ነጥብ 3 በመቶው የኢ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም