ከአድዋ በተጨማሪ የአክሱምና ሽሬ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት አግኝተዋል

50

አዲስ አበባ፤ጥር 11/2013(ኢዜአ) በትግራይ ክልል በጁንታው ጉዳት ደርሶበት የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር ተጠግኖ የአድዋ፣ አክሱምና ሽሬ ከተሞችና አካባቢያቸው ትላንት ማምሻውን የኤሌክትሪክ አገልገሎት አግኝተዋል።

መሠረተ ልማቱን ለመጠገን በተደረገው ከፍተኛ ጥረት ቀደም ሲል አብዛኞቹ የትግራይ ኣካባቢዎች የመብራት አገልግሎት ማግኘታቸውንና የአድዋ ከተማ ደግሞ ትላንት ከሰዓት በፊት ኤሌክትሪክ እንዳገኘ ተገልጿል።

በጁንታው ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሆኖ የቆየው የአክሱምና ሽሬ ከተሞችና አካባቢያቸው የኤሌክትሪክ መስመር በመጠገኑ ከተሞቹ የመብራት አገልገሎት ማግኘታቸውን የኢዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል።

የሑመራ እና ወልቃይት ከተሞችና አካባቢያቸውን ኤሌክትሪክ ለማገናኘትም ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በመሆን የጥገና ስራውን በኋላፊነት ስሜት የተወጡ የተቋሙ ሠራተኞችን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ በተቋሙ ሥራ አመራርና ሰራተኞች ስም ማመስገናቸውን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም