እንግሊዝ በመጪው መስከረም ወር ለሁሉም ወጣት ዜጎቿ የኮሮና መከላከያ ክትባት ለመስጠት ማቀዷን አስታወቀች

1108

ጥር 10/2013(ኢዜአ) እንግሊዝ አሁን ላይ በአማካይ በደቂቃ ለ140 ዜጎቿ የኮሮና መከላከያ ክትባት እየሰጠች መሆኗንና በመጪው መስከረም ወር ላይም እንዲሁ ለመላ ወጣት ዜጎቿ የመከላከያ ክትባቱን ለመስጠት ዕቅድ እንደያዘች ገለጸች።

በእንግሊዝ እስካሁን ለ3.5 ሚሊዮን ዜጎች የመጀመሪያው ዙር ክትባት እንደተሰጠና አሁን ላይ በ24 ሰዓታት ወስጥ 324 ሺህ ክትባቶችን ለመስጠት እየተሰራ መሆኑንም ተጠቅሷል።

ሌሎች ከ5 ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ ክትባቱን ለመውሰድ ለሰኞ ቀጠሮ እንደተያዘላቸው ይፋ ሆናል።

ቀደም ሲል በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በሚገኙ የመድሃኒት መሸጫ ሱቆች ክትባቱ እንዲሰጥ መደረጉንና የክትባት አቅርቦት መስጫ አካባቢዎች ማስፋት ላይ ሀገራቸው አጠናክራ እንደምትቀጥል የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ዶሚኒክ ራዓብ ትላንት መናገራቸው ሲጂቲኤን አፍሪካ የሀገሪቱን የዜና ምንም ጠቅሶ አስነብቧል፡፡

ሚኒስትሩ በቅዳሜ ዕለት ብቻ በመላ ሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ከገባ ጀምሮ ከተመዘገበው ከፍተኛው የእለት የሞት መረጃ 3ኛ ደረጃነትን የያዘ የ1ሺህ 295 ሰዎች የሞት መረጃ ቢመዘገብም በእለቱ የተመዘገበው የ41ሺህ 346 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን በጣም ዝቅተኛ ሲሉም ገልጸውታል፡፡


በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ መገኘቱ ከተነገረ ጀምሮ በእንግሊዝ በስኮትላንድ፣ በዌልስና በደቡባዊ አየርላንድ በ3ኛው ዙር የእንቅስቃሴ ገደብ ውስጥ መሆናቸውንም ነው የተገለጸው።


በየዕለቱ የሚመዘገበውን የሞትና የመያዝ ቁጥር ለመቀነስ በመጪው መስከረም ወር ለሁሉም ወጣት ዜጎች ክትባቱን ተደራሽ ማድረግ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለስካይ ኒውስ መናገራቸውን ዘገባ ያመለክታል፡፡