የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች ኮንፍረንስ በአዳማ እየተካሄደ ነው

1120

አዳማ፤ ጥር 10/2013(ኢዜአ) “የወጣቶች ሚና በሀገር ግንባታ ” በሚል መርህ ሃሳብ የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች በአዳማ አባገዳ አዳራሽ ኮንፍረንስ እያካሄዱ ነው።

ኮንፍረንሱ ወጣቶች የክልሉን ሠላም በማስጠበቅ፣ የፖለቲካ ጽንፈኝነት ለመታገል የሀገርን አንድነት ለማስጠበቅ በሚደረገው እንቅስቃሴ የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያግዝ መሆኑን የኮንፍረንሱ አስተባባሪ ወጣት  ሃይሉ አዱኛ ገልጿል።


ወጣቶች ለውጡን ከዳር ለማድረስ፣ ልማትና ዕድገትን ለማፋጠን፣ ዴሞክራሲና እኩልነት ይበልጥ እንዲጎለብት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል ጭምር ነው ብሏል።


በኮንፍረንሱ ከሁሉም የኦሮሚያ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የወጣት አደረጃጀቶች እየተሳተፉ ነው።