አቶ ስብሃት ነጋ እና አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሃት ቡድን አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

77

አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2013(ኢዜአ) አቶ ስብሃት ነጋ እና አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሃት ቡድን አመራሮች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በዛሬው እለት የቀረቡት የህወሃት ቁልፍ አመራሮች ከነበሩት መካከል አቶ ስብሃት ነጋ፣ አቶ አባይ ወልዱ፣ ዶክተር አብርሃም ተከስተ፣ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ይገኙበታል።

ተጠርጣሪዎቹ በሰሜን እዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በደረሰው ጥቃት እንዲሁም ሌሎች ተደራራቢ የወንጀል ተግባራት የሚፈለጉ መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ገልጿል።

መርማሪ ፖሊስ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት 20 ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቋል።

ፖሊስ በጠየቀው መሰረትም ፍርድ ቤቱ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም