በፕሪሚሪሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባጅፋርን 3 ለ 2 አሸነፈ

1558

አዲስ አበባ፣ ጥር 7/2013 ( ኢዜአ) በሰባተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚሪሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባጅፋርን 3ለ 2 አሸነፈ ።


የሰባተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚሪሊግ የወንዶች እግር ኳስ ጨዋታ ጨዋታ ጅማ አባጅፋር ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን አካሂደዋል።

በጨዋታውም ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በጨዋታው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስቱንም ጎሎች ጌታሀን ከበደ በማስቆጠር ሃትሪክ ሰርቷል።

ጅማ አባጅፋርን ከሽንፈት ያልታደጉትን ሁለቱን ጎሎች ደግሞ ሮባ ወርቁና ቤካም አብደላ አስቆጥረዋል።

ፕሪሚሪሊጉ ዛሬ ከሰዓትም የሚቀጥል ሲሆን ወላይታ ድቻ ከሰበታ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል።