"የሰላም ወግ፤ ብሔራዊ መግባባት ለኢትዮጵያ እድገት" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው የውይይት መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው

66

ወራቤ፤ ጥር 7/2013(ኢዜአ) ሰላም ሚኒስቴር ከወራቤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ያዘጋጀው የውይይት መድረክ "የሰላም ወግ፤ ብሔራዊ መግባባት ለኢትዮጵያ እድገት " በሚል መሪ ሃሳብ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የመርሃ ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ቶፊክ ጀማል የአገር ሰላም የግለሰብ፣ የማህበረሰብና የተቋም ሰላም በማረጋገጥ ላይ የተመሰረተው መሆኑን ነው የገለጹት።

የሰላም ሚኒስቴር ይህን በመረዳት አገር አቀፍ የምክክር መድረክ መጀመሩ የሚያስመሰግነው ብለዋል።

የፍትህ መዛባት፣ ሙስና እና ሥልጣንን ያለ አገባብ መጠቀም ለሰላም ተግዳሮቶች ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ እነዚህን በመዋቅራዊ እውቀት መፍታት ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ፣ የኢትዮጵያ እሴቶች ለብሔራዊ መግባባትና በአገር ግንባታ ሂደት የታሪክ ሚና ዙሪያ የመነሻ ጽሁፍ በታሪክ ምሁራን ይቀርባል ።

በመድረኩ ላይ በአዲስ አበባ ዩዩኒቨርሲቲ የአፍሪካና ኤሲያ ምርምር ማዕከል ረዳት ፕሮፌሰርና የሰላም ሚኒስቴር የፖሊሲ አማካሪ ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ እና ከዞኑ ወረዳዎች የተወጣጡ አመራሮች ተገኝተዋል።


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም