ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ኮንፍረንስ በባህርዳር ከተማ ተጀመረ

74

ባህርዳር፣ ጥር 07/2013(ኢዜአ) "የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓትና ዴሞክራሲ ለህዝቦች መተሳሰብና አብሮነት " በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ኮንፍረንስ ዛሬ በባህርዳር ከተማ ተጀመረ።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው ኮንፍረንሱ ሲጀመር የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው እንዳሉት የኮንፍረንሱ አንዱ ዓላማ የፖለቲካ ሥርዓት አመጣጥን በመፈተሽ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት እንዲያግዝ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው።

ሌላው በሽግግር ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች፣ የህዝቦች የቀደመ አንድነትና መተሳሰብ አስቻይ ጉዳዮች ላይም እንዲሁ። 

በተጨማሪ ህዝቦች እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ለመፍትሄው ሊህቃን መሆናቸውን ለማስገንዘብ ነው ብለዋል። 

በኮንፍረንሱ ሁለት ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ ምሁራን፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች ፣ ሀገር ሽማግሌዎችና ማህበረሰብ አንቂዎች በኮንፍረንሱ እየተሳተፉ ነው።


ቀደም ሲልም ተመሳሳይ ኮንፍረንስ በአዳማ ከተማ መካሄዱ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም