ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮን በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

112

ጥር6/2013 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ጃው ጂዩዋንን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸው ከተነሱት ዋና ጉዳዮች መካከል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ፣ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ወቅታዊ የትግራይ ክልል ሁኔታ፤ በተለይ በክልሉ ያሉ አዳዲስ ክስተቶችን በሚመለከት ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል ፡፡

በውይይት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የጃክ ማ ፋውንዴሽንን ጨምሮ፣ የቻይና መንግስት እና ኩባንያዎች ዓለም አቀፉን ወረርሽኑን ለመዋጋት ላደረጉት ከፍተኛ ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልፀዋል ፡፡

ቻይና ለኢትዮጵያ አንዳንድ ኘሮጀክቶች ለሰጠችው የብድር ፋይናንስ የክፍያ ጊዜ እንደምታራዝመ ተስፋ እንዳላቸው ጠቁመው፣ ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ ላይ ወረርሽኙ የሚያስከትለውን አስከፊ ተጽዕኖ ለማቃለል የሚረዳ መሆኑንም አመልክተዋል ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በአፍሪካ ለሚፈጠሩ ችግሮች የአፍሪካ መፍትሄዎች” የሚለውን መርህ ያስተጋባውን ቻይናን የህዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተ የምትከተለው በመርህ ላይ የተመሠረተን አቋም አድንቀዋል ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ በቅርቡ በትግራይ ክልል ስለተፈጠሩ ክስተቶች በሰጡት ማብራሪያ መንግስት በክልሉ የሕግ የበላይነትን ማስጠበቅ ዘመቻ አድርጎ በስኬት ማጠናቀቁን ገልጸዋል።

ከህግ ማስከበሩ ጎን ለጎን ከዓለምአቀፍ ምግባረ ሴናይ ኤጀንሲዎች ጋር ሰብዓዊ ዕርዳታ ማድረስ የጥረት መቀጠሉን፣ እና በክልሉ የህወሃት ቡድን ያፈራረሳቸው መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል ፡፡

የህወሃት መሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን፣ እንዲሁም ክልሉ ወደ መደበኛ ሁኔታ እየተመለሰ መሆኑን አቶ ደመቀ አክለው ገልፀዋል ፡፡

አምባሳደር ጃው ጂዩዋን በበኩላቸው በኮቪድ-19 አስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር በአጋርነት በመቆሟ የመንግስታቸውን ምስጋና እና አድናቆት ገልፀዋል ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ላደረጉላቸው ገለፃ ምስጋና ያቀረቡት አምባሳደሩ፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት ለማሳደግም እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል ፡፡

አምባሳደሩ በኢትዮጵያ የሚኖራቸው የሥራ ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን የኢትዮጵ መንግሥት የሚቻለውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚደርግላቸው አቶ ደመቀ ቃል መግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም