የህብረተሰቡን የችግር አፈታት የመፍትሄ ሃሳቦችን ለሠላም እሴት ግንባታ ማዋል እንደሚገባ ተመለከተ

93

ባህር ዳር ጥር 6/2013( አዜአ) በየደረጃው ያለው አመራር የህብረተሰቡን የችግር አፈታት የመፍትሄ ሃሳቦችን በማጎልበት ለሠላም እሴት ግንባታ ማዋል እንዳለበት ተመለከተ።

ህብረተሰብ ተኮር የሠላም ምክክር መድረክ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተጀመረ። 

በሠላም ሚኒስቴር የሠላም ግንባታ ዳይሬክተር ጀነራል ወይዘሮ አስማ ረቢ በመድረኩ እንዳሉት ለሠላምና መረጋጋት ጠንካራ ትብብር ፈጥሮ መስራት ይገባል።

የመድረኩ ዓላማ ሀገር በቀል የችግር አፈታት  የሠላም እሴቶችና  ሃሳቦችን በማሰባሰብ  ለአመራር ግብዓት እንዲውል ለማመቻቸት መሆኑን ገልጸዋል።

በየደረጃው ያለው አመራር የህብረተሰቡን የችግር አፈታት የመፍትሄ ሃሳቦችን ለይቶ በማጎልበት ለሠላም እሴት ግንባታ ሥራዎች ማዋል  እንዳለበት አመልክተዋል።

ለዚህ ይረዳ ዘንድም ሚኒስቴሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሠልጠንና በማወያየት ላይ እንደሚገኝ ዳይሬክተር ጀነራሉ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ሠላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ በበኩላቸው ለሠላም መረጋገጥ በሚገጥሙ ችግሮች ዙሪያ ጥያቄና መፍትሄ ፈላጊ ህብረተሰብ መገንባት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ከመድረኩ የሚገኘው ግብዓትም እስከ ቀበሌ ላለው የህብረተሰብ ክፍል  በማወያየት ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እንደሚከናወኑ  ተናግረዋል።

ሠላም ሚኒስቴርና የክልሉ ሠላምና ደህንነት ቢሮ በመተባበር ለሶስት ቀናት ባዘጋጁት የምክክር መድረክ  ከፌደራል፣ ዞንና ወረዳ የተውጣጡ የሠላምና ደህንነት ዘርፍ፣  የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀቶች እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም