የደቡብ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ነገ ይካሄዳል

1579

ሀዋሳ፤ጥር 6/2013(ኢዜአ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት አምስተኛው ዙር ስድስተኛ ዓመት ሶስተኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነገ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ምክር ቤቱ ለአንድ ቀን በሚቆየው አስቸኳይ ጉባኤው የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያጸደቅ ከምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ የሚጠበቅ መሆኑን ዳይሬክቶሬቱ ገልጿል።