ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ፕሮፌሰር ሂሩት ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት ብቁ እጩ ናቸው አሉ

1697

አዲስ አበባ፣ ጥር 1 /2013 ( ኢዜአ)  ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደ ማሪያም ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት ብቁ እጩ መሆናቸውን ገለጹ።

ፕሮፌሰር ሂሩት ኢትዮጵያን በመወከል ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት እጩ ሆነው ቀርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ለፕሮፌሰር ሂሩት ድጋፍ በመስጠቴ ”ደስ ብሎኛል” ነው ያሉት።

የቀድሞ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩት ፕሮፌሰር ሂሩት አሁን ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ናቸው፡፡