የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አምስተኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ያካሄዳል

65

ጋምቤላ፣  ጥር 1/2013 (ኢዜአ) የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አምስተኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ እንደሚያካሄድ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስታወቁ።

አፈ- ጉባኤው አቶ ጁል ናንጋል ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት የምክር ቤቱ አምስተኛ ምርጫ ስድስተኛ የስራ ዘመን አምስተኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ጥር 2 ቀን 2013 በጋምቤላ ከተማ ያካሄዳል ።

አስቸኳይ ጉባኤው በሚኖረው የአንድ ቀን ቆይታ በየእርከኑ የሚገኙ የምክር ቤት አባላት ብዛት ለመሰወን በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት በማድረግ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል ብለዋል።

በጉባኤው ላይ የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ከ250 በላይ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣የሐይማኖት አባቶች፣ የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀት ተወካዮች እንደሚገኙም አፈ-ጉባኤው ገልጸዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም