የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ተኛውን አገር አቀፍ የመጨረሻ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ

213

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30/2013 ( ኢዜአ)  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛውን አገር አቀፍ የመጨረሻ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።

ቦርዱ ታኅሣሥ 16 ቀን 2013 ዓ.ም የቦርዱ አመራሮችና ፖለቲካ ፓርቲዎች በተገኙበት የመጪው አገር አቀፍ ምርጫን ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ለውይይት አቅርቦ እንደነበር አውስቷል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አቅርበው፣ ቦርዱ እጩዎችን ለማቅረብ የሚያስፈልገውን ፊርማ የሕግ መስፈርት ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ ብቻ አገልግሎት ላይ እንዳይውል የተወካዮች ምክር ቤትን ጠይቋል።

በዚህም መሠረት የመጨረሻው የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ይፋ አድርጓል።

በዚሁ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የተግባራቱ አፈጻጸም ያሉበትን ሁኔታ እንደሚያሳውቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም