በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፋሰስ ልማት ሥራ በይፋ ተጀመረ

115

አሶሳ፣ ታህሣሥ 30 / 2013(ኢዜአ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህብረተሰቡን በማሳተፍ በዘመቻ የሚካሄድ ዓመታዊ የበጋ ተፋሰስ ልማት ሥራ ዛሬ በይፋ ተጀመረ።

የልማቱን ሥራ በክልሉ አሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ በመገኘት ያስጀመሩት የክልሉ ርዕስ መስተዳድር ተወካይ አቶ ባበክር ከሊፋ ናቸው።


ዘመቻው በክልሉ አባይ ተፋሰስ አካባቢ የተራቆቱ መሬቶች ላይ እንደሚያተኩር ተገልጿል።


አርሶ አደሮች እና ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

ለሁለት ወራት በሚቆየው ተፋሰስን መሰረት ባደረገው  የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራው ላይ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እንደሚሳተፍ የሚጠበቅ መሆኑን ሪፖርተራችን ከሥፍራው ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም