ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በኒው አፍሪካ መጽሄት 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

1578

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27/2013 ( ኢዜአ) የኒው አፍሪካ መዕሄት በተጠናቀቀው የፈረንጆች ዓመት ከ100 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን አንዱ አድርጎ መረጣቸው።

መጽሄቱ በዝርዝሩ ውስጥ በተለያዩ የስራ መስኮች የተሰማሩ ግለሰቦችን አካቷል።

በዝርዝሩ ከተካተቱ መሪዎች መካከል ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድን ቀዳሚ አድርጎ አስቀምጧቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያና ኤርትራ እርቅ እንዲፈጽሙና በአገር ውስጥ የተለያዩ የለውጥ ሥራዎችን መሥራታቸውን መጽሄቱ አስታውሷል።

በሕዝቦች መካከል ያለው አንድነት እንዲጠናከር መሥራታቸውንም ነው ኒው አፍሪካ የተሰኘው መጽሄት የጠቆመው።