የጀሞ ሁለገብ የገበያ እና የፉሪ የሴቶች ሁለገብ የገበያ ማዕከላት በዛሬው እለት ስራ ጀመሩ

90

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25/2013 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ የጀሞ ሁለገብ የገበያ እና የፉሪ የሴቶች ሁለገብ የገበያ ማዕከላት በምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቀው ስራ ጀመሩ።

ሁለቱን የገበያ ማዕከላት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

የገበያ ማዕከላቱ የስራ እድል በመፍጠር በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ በአካባቢው ያጋጥም የነበረውን የገበያ እጥረትም እንደሚፈታ ገልጸዋል።

ሁለቱ ሁለገብ የገበያ ማዕከላት ከረዥም ጊዜ በፊት የተገነቡ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ስራ ሳይጀምሩ እስካሁን መቆየታቸው ታውቋል።

ሆኖም በዛሬው እለት ወደ ስራ የገቡት አስፈላጊው መሰረተ ልማት ተሟልቶላቸው መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም