የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ በድሬዳዋ የምድር ባቡርንና ኢንዱደትሪዎችን እየጎበኙ ነው

1763

ድሬደዋ ታህሳስ 24/2013 (ኢዜአ) የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በድሬደዋ ከተማ የኢትዮ ጅቡቲ ዘመናዊ የምድር ባቡርንና ኢንዱስትሪዎችን እየጎበኙ ነው።

በከፍተኛ ወጪ የተገነባው የባለሶስት እግር የ”ቲቪኤስ” ታክሲ መገጣጠሚያንም  የጉብኝቱ አካል ነው።

በጉብኝቱ  የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አህመድ መሐመድ እና የካቤኔ አባላት እየተሳተፉ ነው።

ሚኒስትሯ ነገ በሚካሄደው አራተኛው የእግረኞች እና  ብስክሌተኞች ማበረታቻ መርሃግብር እና የእግር ጉዞ ላይ እንደሚሳተፉ የሚጠበቅ መሆኑን ሪፖርተራችን ከድሬደዋ ዘግቧል።