አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ያሠለጠናቸው የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ

184

አርባ ምንጭ ታህሳስ 24/2013 (ኢዜአ) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ዶክትሬት ያሠለጠናቸው 87 ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ፡፡

በምረቃው ሥነ-ሥርዓት በክብር እንግድነት የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳህሬላ አብዱላሂ ባደረጉት ንግግር "የሀገር ልማትና ብልጽግና ለማረጋገጥ የዜጎችን ጤና መጠበቅና ማበልጸግ ተኪ የሌለው ነው ጉዳይ "ብለዋል፡፡

የጤና ባለሙያዎች ለህዝቡ   የሚኖራቸው ሽፋን  46  ለ10ሺ የሚጠበቅ እንደሆነ ገልጸው  በሀገሪቱ ያለው  10 ለ10ሺህ  እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በጤናው ልማት ዘርፍ ከደረስንበት ዘመን ጋር ሊመጥን የሚችል   የሰው ኃይልን ለመገንባት መንግስት እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ተመራቂዎቹ በተሠማሩበት መስክ የሚገጥማቸውን ችግሮች በመቋቋም  ህዝቡን በቅንነት እንዲያገለግሉም መለዕክታቸውን  አስተላልፈዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ በበኩላቸው ተመራቂዎቹ ሀገሪቱን ከድህነት ለመውጣት የሚደረገው ጥረት  በመደገፍ  በሙያቸው  ሊያበረክቱት የሚችሉ አስተዋጽኦ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ከዛሬው ተመራቂዎች መካከል 32 ሴቶች ሲሆኑ  ዩኒቨርሲቲው  እነዚህን ጨምሮ  እስካሁን 572 የህክምና ዶክተሮችን እንዳስመረቀ ተገልጻል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም